image
image
image
image
image

የክላስተር 3 የምግብና ጤና ነክ ተቋማት የብቃት ማረገጥ ጽ/ቤት የብቃት እና የእድሳት ስራን በኦላይን ለማግኘት አገልግሎትን አሰጣጡን የሚያግዝ በዲጅታል አገልግሎት መረብ መጀመሩን ጽ/ቤቱ አስተዋወቀ

ሰኔ 1, 2018
በአዲስ አበባ ምግብ መድሃኒት ባለስልጣን የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የክላስተር -3 ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የምግብና ጤና ነክ ተቋማት የብቃት መረጋገጫ ፍቃድን በኦላይን ለማግኝት እና ለመመዝገብ የሚያግዝ የምግብና መድሃኒት የዲጅታል አገልግሎት መረብ አስተዋወቀ ፡፡ ተቋማት አዲስ የብቃት ማረጋገጫ ለመዉሰድ ፣ለማደስ እንዲሁም ምዝገባዎችን ለማከነወን የዲጅታል አገልግሎት መረብ መጠቀማቸዉ አገልግሎት ለማግኘት ወደ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በአካል ሲመጡ የሚወስድባቸው ጊዜና የሚያወጡት ገንዘብ በማስቀረት በተቀላጠፈና ስታንዳርዱን በጠበቀ መልኩ አገልግሎት እንዲያገኙ እገዛዉ የጎላ ነዉ ሲሉ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የክላስተር -3 ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ነፃነት ገ/ፃድቃን ተነግሯል ። በመርሃ-ግብሩ ላይ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የክላስተር -3 ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የጤናና ጤና ነክ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ብቃት መረጋገጫ ቡድን መሪ አቶ አለመየሁ ወርቁ እንደገለጹት ነዋሪዎች በቀላሉ ባሉበት ቦታ ሆነው የምግብና ጤና ነክ ተቋማት የብቃት መረጋገጫ ፍቃድን በኦላይን ለማግኝት እና ለመመዝገብ የምግብና መድሃኒት የዲጅታል አገልግሎት መረብ መጠቀመም ይቻላል ብለዋል ፡፡ ከዚህም ጋር አያይዘዉ የብቃት ማረጋገጫ አገልግሎት አሰጣጥ ለማግኝት የዲጅታል አገልግሎት መረብ ላይ አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶች፡-የአንድ ድርጅት መመስረቻ ሰነድ፣የታደስ የንግድ ፍቃድ ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN NUMBERር/፣የቦታዉ ካርታ ወይም የኪራይ ዉል ስምምነት የጽ/ቤቱን የዲጅታል ስርዓ ተጠቅሞ መመዝገብ እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡ የጽ/ቤቱን የድረ -ገጽ አገልግሎት ለማግኛት እና ዝርዝር መመሪያዎችን ለማንበብ ወደ www.aafdanslc3.gov.et ድር ገጽ ጎራ ይበሉ ሲሉ አስተዋዉቀዋል፡፡

መልዕክትዎን ይላኩ